የሳንባ ካንሰር ምርመራ
Fred Hutchinson Cancer Center እና UW Medicine በጋራ ለሳንባ ካንሰር በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ምርመራ ያቀርባሉ። ዝቅተኛ መጠን ያለው የሚሰላ ቲሞግራፊ (CT) ተብሎ የሚጠራው ቀላል እና ፈጣን ምርመራ ለበሽታው የሚመከር ብቸኛው የማጣሪያ ምርመራ ነው። ቀደም ብሎ ሲታወቅ፣ ከታወቀ ካንሰር የመዳን መጠኖች በከፍተኛ ሁኔታ ይሻሻላሉ።
ቀጠሮ ለማስያዝ ይጠይቁ
ለምርመራ ብቁ እንደሆኑ ካመኑ እባክዎ ለምርመራ ትእዛዝ ለማግኘት የመጀመሪያ እንክብካቤ ዶክተርዎን ያነጋግሩ።
ትዕዛዞችን በፋክስ ቁጥር (206) 606-6729 መላክ ይቻላል።
የCT የሳምባ ካንሰር ምርመራ ማዘዣ ቅጽ (PDF)
አንዴ ማዘዣ ከተሰጥዎ እና ቀጠሮ ለማስያዝ ዝግጁ ከሆኑ በኋላ ወይም የሳምባ ካንሰር ምርመራ ፕሮግራማችንን በተመለከተ ማንኛውም ጥያቄዎች ካሉዎ እባክዎ በስልክ ቁጥር (206) 606-1434 ይደውሉልን።
በመላው Puget Sound ስድስት አመቺ ቦታዎችን እናቀርባለን፡
- Fred Hutchinson Cancer Center - South Lake Union
- UW Medical Center - Montlake
- UW Medical Center - Roosevelt
- UW Medical Center - Northwest
- Harborview Medical Center
- UW Medicine Eastside Specialty Center
የአገሬው ተወላጆችን ጤና ለማሳደግ SCCA የሳንባ ካንሰር ምርመራን ለማበረታታት በክልላችን ያሉ የጎሳ ብሄሮች እና ተወላጆች ጋር ለመድረስ የሚያስችል የጤና ፕሮግራሙን አቋቁሟል።
ምርመራ ማድረግ ይኖርብኛል?
ሁሉም ከዚህ በታች የተመለከቱት እውነት ከሆኑ መደበኛ ምርመራ ቢያደርጉ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
- ዕድሜዎ በ50 እና 80 ዓመታት መካክል ከሆነ።
- በአሁኑ ወቅት የሚያጨሱ ከሆነ ወይም ባለፉት 15 ዓመታት ውስጥ ማጨስ ካቆሙ።
- ለ20 ዓመታት በአማካኝ ቢያንስ በቀን 1 ፓኬት ወይም ለ10 ዓመታት በቀን 2 ፓኬት ያጨሱ ከነበረ።
እ3ነዚህ የሳምባ ካንሰርምርመራ መመሪያዎች የወጡት በዩ.ኤስ የመከላከል አገልግሎቶች የተግባር ሀይል/U.S. Preventive Services Task Force (USPSTF) ነው።
ተጨማሪ የምርመራ መስፈርት
ዕድሜያቸው 50 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ እና ለ20 ዓመታት ወይም ከዚያ በላይ በቀን 1 ፓኬት ያጨሱ የነበሩ ሰዎች ከሚከተሉት የስጋት ምልክቶች መካከል አንዱ የሚታይባቸው ከሆነ ምርመራ ስለማድረግ ማሰብ አለባቸው:
- ከፍተኛ የተመዘገበ ለራደን ጨረር ካለብዎ።
- በስራ ምክንያት ለሲሊካ፣ ካድሚየም፣ ኦቤስቶስ፣ አርሰኒክ፣ ቤሪሊየም፣ ክሮሚየም፣ ኒኬል ወይም የናፍጣ ጭስ ከተጋለጡ።
- በሳምባ ካንሰር፣ ሊምፎማ ወይም የጭንቅላትና አንገት ካንሰር ተይዘው ከተረፉ።
- ስር የሰደደ የሳምባ በሽታ ወይም የሳምባ ፋይብሮሲስ ታሪክ ካለብዎ።
- በቤተሰብ የሳምባ ካንሰር ታሪክ ካሉዎ።
በሁለተኛው የከፍተኛ ስጋት ቡድን ስር የሚመደቡ ታካሚዎች በብሔራዊ የሳምባ ምርመራ ሙከራ (National Lung Screening Trial) ከተጠኑት ጋር ተመሳሳይ ስጋቶች ይታዩባቸዋል። ነገር ግን በጥቅሉ በተካሄደ ሙከራ የተገኘ መረጃ ስለሌለ ይህ ቡድን ከCTምርመራ ምን ያክል እንደሚጠቀም ሙሉ በሙሉ አይታወቅም።
በሌሎች ማጨስ ምክንያት ተጋላጭ መሆን የሳምባ ካንሰር CT ምርመራ ለማድረግ እራሱን የቻለ ስጋት አይደለም።
የምርመራ ምንጮች
- የሳምባ ካንሰር ስጋትዎን በፈጣን የኦንላይን የዳሰሳ ጥናት ያስሉ። ጥናቱን ለማግኘት እዚህ ላይ ይግቡ
- በሳምባ ካንሰር ምርመራ ላይ ከSCCA ሀኪሞች ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ያዳምጡ። እዚህ ላይ ያዳምጡ
ምርመራው ምንን ይይዛል?
ምርመራው ፈጣን፣ ቀላል፣ ህመም የማይፈጥር ሆኖ ሙሉ ልብስዎን እንደለበሱ ሊመረመሩ ይችላሉ። የአነስተኛ ዶዝ CT ምርመራ በማሽኑ ውስጥ እና ወደ ማሽኑ በሚንሸራተት ጠረጴዛ ላይ እንደተኙ ብዙ ምስሎችዎን የሚወስድ ልዩ የራጅ ምርመራ አይነት ነው። ከዚያም ኮምፒውተር እነዚህን ምስሎች ከሳምባዎ ዝርዝር ምስሎች ጋር ያጣምረዋል።