የጡት ካንሰር ምርመራ
የሲያትል የካንሰር እንክብካቤ አሊያንስ (SCCA) የሚገኙ የጡት ጤንነት ባለሙያዎች የጡት ካንሰር ምርመራ የሚያቀርቡ ሲሆን በእድሜዎ፣ በጤንነትዎ፣ በአደጋ ደረጃዎ፣ እና ሌሎች መስፈርቶች ላይ በመመርኮዝ የትኛው ምርመራ ለእርስዎ ተስማሚ እንደሆነ በማወቅ ሊረዱዎ ይችላሉ።
የህክምና ምርመራዎች ምንም አይነት የጡት ካንሰር ምልክቶች ለሌላቸው ሴቶች በመደበኛ ፕሮግራም ይደረጋሉ። እነዚህ ምርመራዎች ሳይታዩ ሊታለፉ ይችሉ የነበሩ ምልክቶችን ይለያሉ።
ይሄ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ቀድመን በሽታውን ባወቅን ቁጥር የተሸላ ነው። አነስተኛ፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጡት ካንሰር ያለባቸው ሴቶች ብዙ የህክምና አማራጮች እና ከፍተኛ የመዳን እድል አላቸው።
ለምን SCCAን ለምርመራ መምረጥ እንዳለብዎ
እኛ የምንመክራቸው የጡት ካንሰር የህክምና ምርመራዎች—ማሞግራፊ እና፣ ለአንዳንድ ሴቶች የጡት MRI—በምርጥ ሳይንሳዊ ማስረጃዎች ላይ የተመረኮዙ ናቸው፣ ለምሳሌ SCCA እንደሚያቀርባቸው ሁሉም እንክብካቤዎች።
- SCCA በአሜሪካ የራዲዮሎጂ ኮሌጅ የጡት ኢሜጂንግ የልቀት ማዕከል እውቅና ተሰጥቶታል።
- ምርመራዎችዎን የሚያደርጉት እና የሚተነትኑት ቴክኖሎጂስቶች እና ራድዮሎጂስቶች በጡት ምስል ላይ በብቃት የተካኑ ስለሆኑ በ SCCA ምርመራ ሲያደርጉ በራስ የመተማመን ስሜት ሊኖርዎት ይችላል። ራዲዮሎጂስቶቻችን የ UW ህክምና ዶክተሮች ናቸው።
- እንደ 3D ማሞግራፊ ያሉ ግንባር ቀደም ቴክኖሎጂዎችን የምንጠቀም ሲሆን፣ ምስል በመጠቀም የጡት ካንሰር በጊዜ ለመለየት ምርምርን በንቃት በማካሄድ ላይ እንገኛለን።
- ለአእምሮዎ ሰላም እንዲሰጥዎት ለማስቻል፣ በዚያው እለት የምርመራዎን ውጤት የምንሰጥበት ቀጠሮ የመምረጥ አማራጭ አለዎት።
- ራዲዮሎጂስትዎ ያልተለመዱ የሚመስሉ ህብረ ህዋሳትን ለመመርመር ባዮፕሲን ከመከረዎት፣ በዚያኑ ቀን የባይዮፕሲ አገልግሎቶችን እናቀርባለን።
ማሞግራፊ
የምርመራ ማሞግራሞች እጅግ የተለመዱ እና እጅግ የተጠኑ የጡት ካንሰር የህክምና ምርመራዎች ናቸው። ካንሰርን በጊዜ በመለየት ህይወትን ያተርፋሉ።
- ማሞግራም ራዲዮሎጂስት እርስዎ ወይም የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ልትገነዘቧቸው ያልቻላችኋቸውን ትንሽ የሆኑ ያልተለመዱ ነገሮችን እንዲያይ የሚያስችለውን የጡትዎን ምስል ለመፍጠር X-ሬይ ይጠቀማል።
- በSCCA ውስጥ፣ 3D ማሞግራፊ ወይም ዲጂታል የጡት ቶሞሲንተሲስ የሚባል እጅግ የላቀ የማሞግራፊክ ቴክኖሎጂን እንጠቀማለን።
- 3D ማሞግራፊ ብዙ የጡትዎን ፎቶግራፎች በአንድ ጊዜ ይወስዳል። ይሄ ማለት በጊዜ እውነተኛ ካንሰርን እና ጥቂት ሀሰተኛ የሆነ የበሽታ ምልክትን (ጤናማ በሆነ ህብረ ህዋስ ውስጥ ካንሰር አለ ብሎ መጠራጠር) የማግኘት የተሻለ እድሎች አሉት ማለት ነው።
- አንዴ ማሞግራም ካደረጉ፣ ጥቅጥቅ ያለ ጡት እንዳለዎት ሊረዱ ይችላሉ። ይህ መረጃ ግራ ሊያጋባ ስለሚችል፣ ስለ ጡት ጥግግት እና ማወቅ ስላለብዎት መረጃ እዚህ አለ።
ቦታዎች
በርካታ ምቹ ቦታዎችን እናቀርባለን:
- SCCA የሴቶች ማዕከል በSCCA South Lake Union ውስጥ
- SCCA የማሞግራም ቫን (የተለያዩ ሞታዎች)ቦታዎች)
- SCCA በ UWMC-Northwest ውስጥ
- UWMC-Roosevelt
- UW Eastside Specialty Center
የማሞግራም ወይም የጡት MRI ቀጠሮ ይያዙ
ስልክ (206) 606-7800
ኢሜይል imagingsched@seattlecca.org
በቅርብ ዝግጅት ላይ የማሞግራም ቫን ስለመኖሩ ለመጠየቅ እባክዎን ከላይ ባለው ቁጥር ይደውሉ።
3D ማሞግራፊ
SCCA ለሁሉም ታካሚዎች እንደ መደበኛ የማሞግራፊ ምርመራ ዲጂታል የጡት ቶሞሲንተሲስ ወይም DBT በመባል የሚታወቅ 3D ማሞግራፊ ያቀርባል። ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዶክተሮች የጡትዎን ህብረ ህዋስ በበለጠ ጥልቀት፣ አንድ በአንድ ንብርብር እንዲመረምሩ ያስችላቸዋል።
በ 2D (የተለመደው) ማሞግራፊ፣ የጡትዎ አንድ ምስል ከላይ እና አንድ ምስል ደግሞ ከጎን ይወሰዳል። 3D ማሞግራፊ የጡትዎን ብዙ ምስሎች ከሁለቱም አንግሎች የሚወስድ ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው 1 ሚሊሜትር ብቻ ውፍረት ወዳላቸው ንብርብሮች ክምር ወይም “ቁርጥራጮች”ለመቀየር ከፍተኛ ሀይል ያለው ኮምፒውተርን ይጠቀማል።
ይህ ማለት ራዲዮሎጂስትዎ የጡት ካንሰሮችን በበለጠ በግልጽ ማየት እና በበለጠ በራስ መተማመን ግምገማ ሊያቀርብልዎ ይችላል። 3D ማሞግራፊ በእውነቱ የተለመደ የሆነ ነገር ግን በ 2D ምስል ላይ ያልተለመደ ሊመስል የሚችል የህብረ ህዋስ ተከታታይ ምርመራ አስፈላጊነትን ሊቀንስልዎ ይችላል።
የ 3D ማሞግራም ማድረግ የ 2D ማሞግራም ከማድረግ ጋር እጅግ ተመሳሳይ ነው። በልዩ ሁኔታ የሰለጠነ ቴክኖሎጂስት ጡትዎን በልዩ መድረክ ላይ ያስቀምጣል እና እንደ መቀዘፊያ ባለ ነገር ስር ይጨምቀዋል። የ X-ሬይ ክንዱ ብዙ ምስሎችን በማንሳት በጡትዎ ላይ ያልፋል።
SCCA የማሞግራም ቫን
ማሞግራም በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ የ SCCA ማሞግራም ቫን በ Puget Sound አካባቢ ያልፋል። የ SCCA ማሞግራም ቫን በአካባቢዎ መቼ እንደሚኖር ለማየት የጊዜ ሰሌዳችንን ይመልከቱ።
SCCA Mammogram Van Schedule (PDF)
ስልክ (206) 606-7800
የጡት ማግኔቲክ ሪዞናንስ ምስል (MRI)
የጡት MRI የጡት ካንሰርን ለመለየት እና በበሽታው አዲስ ለተያዙ ሴቶች ምርጥ ህክምናዎችን ለማቀድ ሀይለኛ መሳሪያ ነው። MRI ለአንዳንድ ሴቶች አስፈላጊ የሆነ ተጨማሪ የህክምና ምርመራ ነው። የጡት MRI ጡቶችን ለመሳል ከ X-ሬይ ይልቅ ጠንካራ ግኔቲክማግኔቲክ ፊልድ ይጠቀማል። በማሞግራም ለማየት የሚያዳግቱ የጡት ካንሰሮችን ለመለየት ይረዳል።
- በአጠቃላይ፣ በጡት ካንሰር የመያዝ ተጋላጭነትዎ ከፍተኛ ከሆነ፣ ከማሞግራም ጋር አብሮ የጡት MRI ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው።
- የ SCCA ራዲዮሎጂስቶች ከፍተኛ ጥራት ያለው የጡት MRI ምስሎችን በማግኘት እና የትኞቹ ሴቶች ከ MRI የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በመለየት የተካኑ ናቸው።
- እንዲሁም ይህንን ቴክኖሎጂ በተሻለ መንገድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚፈትሹ የጡት MRI ምርምሮች እና የክሊኒክ ሙከራዎች እናካሂዳለን።
የጡት MRI ቀጠሮ ይያዙ
ቀጠሮ ለመያዝ የሚፈልጉ ከሆነ ወይም ስለጡት ካንሰር ተጋላጭነትዎ እርግጠኛ ካልሆኑ እና የጡት MRI ለእርስዎ ትክክል መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ፣ ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ጋር ይነጋገሩ ወይም እኛን ያነጋግሩን።
ስልክ: (206) 606-7800
ሌሎች የጡት ምስል ምርመራዎች
የ SCCA ባለሙያዎች የጡት ካንሰርን ለመመርመር ስላሉት ምርጥ መንገዶች የቅርብ ጊዜንጊዜ ሳይንሳዊ ማስረጃን በየጊዜው የሚገመግሙ ስለሆነ፣ ማንኛውም እኛ የምናቀርበው ምርመራ ከአደጋው ጥቅሙ እንደሚያመዝን እርግጠኛ መሆን ይችላሉ።
ማሞግራፊ እና MRI በምስል የጡት ካንሰርን ለመለየት በግምባር ቀደምነት የተረጋገጡ መንገዶች ናቸው።
ጥቅጥቅ ያሉ ጡቶች ያላቸውን ሴቶች ለመመርመር ሌሎች የምስል ምርመራዎች ጥቅም ላይ ሲውሉ ወይም ሲጠኑ ሊሰሙ ይችላሉ። ከእነዚህ ሌሎች ምርመራዎች አንዳቸውም ህይወትን ስለማዳናቸው አልተረጋገጡም። ለዚህም ነው በ SCCA ያሉ ዶክተሮች ለብዙ ሴቶች በመደበኛነት የማይመክሯቸው።
ከማሞግራፊ እና ከጡት MRI ውጪ ሊሰሟቸው የሚችሉ በጣም የተለመዱ የህክምና ምርመራዎች እነዚህ ናቸው:
- የአልትራሳውንድ ምርመራ: አልትራሳውንድ በማሞግራም ላይ የተገኘውን እብጠት ወይም አጠራጣሪ አካባቢ በተሻለ ለመመልከት በጣም ጥሩ መሳሪያ ነው። ነገር ግን ምልክቶች የሌላባቸውን ሴቶች ለመመርመር በአጠቃላይ እንደሌሎቹ መንገዶች ጠቃሚ አይደለም። ይህም ከሚለያቸው ትክክለኛ የካንሰር ቁጥሮች ጋር ሲነጻጸር ብዙ ሀሰተኛ የሆነ የበሽታ ምልክቶች (ካንሰር ሳይሆኑ የሚቀሩ አጠራጣሪ አካባቢዎች) ስለሚፈጥር ነው። በ SCCA ውስጥ፣ በዋናነት በከፍተኛ ተጋላጭነት ላይ ላሉ እና በሌሎች የህክምና ጉዳዮች ምክንያት MRI ማድረግ በማይችሉ ሴቶች የአልትራሳውንድ ምርመራ እንጠቀማለን።
- ሞለኪዩላር የጡት ምስል፣ ጡት-ተኮር ጋማ ምስል (BGSI) (scintimammography ተብሎም ይጠራል) እና ፖሲትሮን የሚለቅ ማሞግራፊ (PEM) ጨምሮ: ከማሞግራፊ ጋር ሲነጻጸር፣ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ሴቶችን የጤና አደጋ ሊያመጡ ለሚችሉ ከፍተኛ የጨረር መጠን ያጋልጣሉ። ምንም እንኳን አንዳንድ ማዕከላት BGSI እና PEM ቢሰጡም፣ እነዚህን ምርመራዎች እንዴት መጠቀም እንዳለብን ለመወሰን ተጨማሪ ምርምር ያስፈልጋል።
- ያጠረ ወይም ፈጣን MRI: ይህ አጭር የጡት MRI ምርመራ ከማሞግራም ጋር አብሮ ጥቅም ላይ ሲውል ጥቅጥቅ ያሉ ጡቶች ባላቸው ሴቶች ላይ ካንሰርን ለመለየት ይረዳል። ማን ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ ይህንን ቴክኖሎጂ በንቃት እያጠናን ነው።
- በንጽጽር-የተሻሻለ ማሞግራፊ: ከማሞግራምዎ በፊት በደም ስርዎ ውስጥ የንጽጽር ወኪልን ማስገባት ካንሰር እንዲለይ ሊያደርግ ይችላል። በምስሉ ውስጥ የሚበራው የንጽጽር ወኪሉ፣ እንደ እጢዎች ባሉ ያልተለመደ ከፍተኛ የደም ፍሰት ባለባቸው አካባቢዎች በቀላሉ ይጠራቀማል። እንደዚህ አይነት ምርመራዎችን እናጠናለን።
- ቴርሞግራፊ: ለማሞግራፊ እንደ አማራጭ መጠቀምን በመቃወም የምግብ እና የመድሀኒት አስተዳደር በሰጠው ምክር መሰረት SCCA የቴርሞግራፊ ምርመራዎችን አይሰጥም።
የጡት የራስ ምርመራ እና ግንዛቤ
በጡቶችዎ ላይ በተለምዶ ምን እንደሚሰማዎት በማስተዋል እና ስለሚመለከቷቸው ማንኛውም ለውጦች የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን በማናገር የጡት ካንሰርን ለመለየት እርስዎ ሊረዱ ይችላሉ። አብዛኛዎቹ የጡት ካንሰሮች ዛሬ ላይ በራስ የሚለዩ ናቸው።
በአሜሪካ፣ በጡት ካንሰር ከተያዙ እያንዳንዳቸው 10 ሴቶች መካከል:
- ስድስቱ በሽታው የተገኘባቸው ምንም ምልክቶች ሳይኖራቸው ያልተለመደ የህብረ ህዋስ ያሳየ እንደ ማሞግራም ያለ የምርመራ ሙከራ አድርገው ስለነበር ነው።
- አራቱ በሽታው የተገኘባቸው ሴትዋ ወይም የጤና እንክብካቤ አቅራቢው እብጠት ስለተሰማቸው ወይም ሌላ ምልክት ስላስተዋሉ እና ስለተመረመረችስለተመረመሩ ነው።